ABSTRACT

The profound importance of field practicum in social work education is to help students learn in a professional setting, demonstrate skill, and integrate the theories and practices learned in and out of the classrooms. Fieldwork practicum is, therefore, a hallmark of social work to advance the values and practices of social work education. The primary objective of this chapter is to present the views of students, agency liaisons, and instructors’ on field practice in Ethiopia. The study selected informants purposively based on their knowledge and affiliation with the field practicum. The findings show that students learn social work in culturally sensitive settings, working with diverse and at-risk populations. It further shows that it introduces and teaches them about indigenous knowledge and the value of helping people in real-life situations. However, the learning process is affected by a lack of commitment from the instructors’ side, weak supervision of the agency liaisons, and students’ hesitancy. The lack of mutual understanding of shared values between actors in field practicum has been identified as the source of challenges and suggests developing a new curriculum across Ethiopia.

በሶሻል ዎርክ ትምህርት የመስክ ልምምድ ዋናው አላማ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የተማሩአቸውን የንድፈ ሀሳብ እውቀቶች በእውኑ አለም ምን አንደሚመስሉ ለማየት የሚረዳቸውን መልካም አጋጣሚ መፍጠር ሲሆን ለሶሻል ዎርክ ትምህርት መሰረትም ነው፡፡ ስለዚህ የመስክ ልምምድ የሶሻል ዎርክ እሴቶችንና ተግባራትን የበለጠ ለማጎልበት የሚረዳ የሙያው ወሳኝ ክፍል ነው ተብሎ ይወሰዳል፡፡ የዚህ ምዕራፍ ዋናው ዓላማ የሶሻል ዎርክ ተማሪዎችን፣ ከተቋማት የሚመደቡ ቱተሮችንና የሶሻል ዎርክ ትምህርት ቤት መምህራንን እይታ ከመስክ ትምህርት አንጻር ማየት ነው፡፡ ጥናቱም ከመስክ ልምምድ ትምህርት ጋር ቅርበትና እውቀት ያላቸውን መረጃ ሰጪዎች ለይቶ መርጦአል፡፡ የጥናቱ ግኝትም ተማሪዎች በብዝሀ ባህልና ልማዶች ውስጥ እንዴት መስራትና ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የተለያዮ ሰዎችን መርዳት እንደሚቻል ለመረዳት አስችሎአቸዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በእውነታው አለም ውስጥ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ አስገብቶ ርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን እንዴት መርዳት እንደሚችሉም አሰተምሮአቸዋል፡፡ የሀገር በቀል እውቀቶችን ፋይዳም እንዲረዱ ረድቶአቸዋል፡፡ ነገር ግን የመስክ ትምህርት ሂደቱ ተግዳራቶች ያጋጠሙት ሲሆን መነሻቸውም የመምህራን ትኩረት ማነስ፣ ከተቋማት የሚመደቡ ረዳቶች ክትትል የላላና ተማሪዎች ለመስክ ልምምዱ የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆን ናቸው፡፡ ጥናቱ በመስክ ልምምድ ላይ የሚሳተፉ ወሳኝ ሰዎች የሶሻል ዎርክ እሴቶችን በእኩል ደረጃ ያለመረዳት ለተግዳሮቶቹ መነሻ መሆናቸውንም ለይቶአል፡፡ በመጨረሻም የሶሻል ዎርክ መምህራንን፣ የስርዐተ ትምህርት ቀራጮችንና ተቋማትን አንድ ላይ በማገናኘት በስራ ላይ ያለውን ካሪኩለም በመከለስ አውዱን የዋጀ ካሪኩለም ቢዘጋጅ የሚል ምክረ ሀሳብ ሰጥቶአል፡፡